የህዝብ ግንኙት ባለሙያ (Public relation officer)

መሰረት ሞላ

የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ

ዝርዝር የስራ ተግባራት ኃላፊነት

  1. የማህበሩን የስራ እንቅስቃሴ መጽሄቶችን፣ ጋዜጦችን፣ በራሪ ጹሁፍችን፣ ዜናዎችን እንዲያዘጋጅና እንዲታተም ያድርጋል ስርጭቱን ይቆጣጠራል /ትቆጣጠራለች/ ፡፡
  2. በማህበሩ አላማ ዙሪያ/ሴቷን በተመለከተ/ አዳዲስ ሳይንስና ቴክኖሎጅ ፈጠራዎችን ግኝቶችን ዜናዎችን ለአባላቱ አመች በሆነ መንገድ ያስተላልፋል/ታስተላልፋለች/፡፡
  3. ማህበሩ ስለሚያዘጋጃቸው ስብስባዎችና ጉባኤዎች ፖስተሮች፣ ማይክራፎኖች፣ ዲኮሬሽኖች ያዘጋጃል፣ የስብሰባ ትውውቅ ያደርጋል፣ የመስተንግዶ ስራዎች በኮሚቴነት ያከናውና/ታከናውናለች/ ፡፡
  4. ማህበሩ ከአቻ ማህበራት ጋር ግንኙነት እንዲፈጥር ቅድመ ሁኔታዎችን ያመቻቻል/ታመቻቻለች/፡፡
  5. በማህበሩ ስም የሚዘጋጁ የጥሪ ወረቀቶችን በወቅቱ መሰራጫታቸውን ይከታታል/ትከታተላለች/፡፡
  6. የማህበሩ እንግዶች በሚመጡበት ወቅት ከሚመለከታቸው ጋር በመተባበር የስራና የመስተንግዶ ፕሮግራም ያወጣል፣ በማህበሩ ሊቀመንበር ሲፈቀድ በስራ እንዲተረጎም ያደርጋል/ታደርጋለች/፤
  7. የማህበሩን እንቅስቃሴ የሚመለከቱ የህዝብ ግንኙነት ሥራዎች ጥያቄዎች ሲያቀርቡ ጉዳዩን ለማህበሩ ኃላፊዎች አቅርቦ ምላሽ እንዲያገኙ ያደርጋል/ታደርጋለች/፡፡
  8. ጠቃሚ ተሞክሮዎችንና መረጃዎችን በማሰባሰብ ለማህበሩ ሊቀ-መንበር ያቀርባል፣ በጥራዝ ያዘጋጃል፣ አስፈቅዶ ለአባለት ያስተላልፋል/ታስተላልፋለች/፡፡
  9. የማህበሩን የኮምፒውተር እና ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ጥገና እና ሰርቪስ ማድረግ፡፡
  10. የኮምፒውተር የሲስተም ልማት እና የሶፍትዌር ልማት እና ጥገና ስራዎችን ይሰራል /ትሰራለች፡፡
  11. የሁሉም የስራ ክፍል የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች አስፈላጊው ጥበቃ እና እንክብካቤ እንዲደረግላቸው ክትትልና ድጋፍ ያደርጋል/ታደርጋለች፡፡
  12. ለማህበሩ ሰራተኞች የኮምፒውተር ሳይንስ እና ልዩ ልዩ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች አጠቃቀም ተከታታይ አጫጭር ስልጠናዎችን ይሰጣል /ትሰጣለች፡፡

 

 

  1. የማህበሩን የኢንተርኔት አገልግሎት ቀልጣፋ እንዲሆን የመስመር ዝርጋታ እና ሌሎች ተያያዥ ሙያዊ ድጋፎችን ታደርጋለች/ያደርጋል፡፡
  2. የማህበሩን ድህረ-ገፅ እና ማህበራዊ ሚዲያ ያለማል፣ ያስተዳደርለ፣ ወቅታዊ ጉዳዮች እና ልዩ ልዩ የማህበሩ ክንውኖች ለማህበረሰቡ ተደራሽ እንዲሆኑ ያደርጋል፡፡
  3. የማህበሩን ፎቶ ካሜራ ወጭ በማድረግ በጥንቃቄ ይይዛል/ትይዛለች፣ ለተረከበው ዕቃም አስፈላጊው ጥንቃቄ እና ሰርቪስ እንዲደረግለት ያደርጋል/ታደርጋለች፡
  4. አስፈላጊ ሁኖ በተገኘበት ጊዜ ሁሉ የማህበሩን የስራ እንቅስቃሴ፣ የአባላትን ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት፣ ልዩ ልዩ ስብሰባዎችን በሙሉ የፎቶ ግራፍ እና የቪዲዮ ቀረፃ ስራ ይሰራል/ትሰራለች፡፡
  5. ማህበሩ በሚያካሂዳቸው ልዩ ልዩ ስብሰባዎች፣ የማህበሩ ጉባኤ፣ ምክር ቤት እና ልዩ ልዩ ስልጠናዎች ላይ በመገኘት የማይክራፎ፣ የፕሮጀክተር፣ እንዲሁም የኤሌክትሮኒክስ ቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ይሰራል፣ በአግባቡ መሟላታቸውን እና ለስራ ዝግጁ መሆናቸውን ይከታተላል፣ ያረጋግጣል፡፡
  6. የማህበሩን መደበኛ ጉባኤ፣ የምክር ቤት ስብሰባ፣ እንዲሁም ሌሎች ስብሰባዎች እና አስፈላጊ ሁኖ ሲገኝ በመስክ በመንቀሳቀስ ልዩ ልዩ ዝግጅቶችን እና የአባላትን እንቅስቃሴ በፎቶ እና በቪዲዮ ይቀርፃል/ትቀርፃለች፡፡
  7. የሚቀረፁ ዶክሜንቶች በአግባቡ እና ግልፅ በሆነ መንገድ ተደራጅተው እንዲያዙ ያደርጋል/ታደርጋለች፡፡
  8. የተቀረፁ ዶክሜንቶች በሚቀናበሩበት እና በሚዘጋጁበት ወቅት ከሚመለከተው ባለሙያ ጋር ሁኖ በጋራ ይሰራል/ትሰራለች፡፡
  9. የሚገኙ መልካም ተሞክሮዎችን በመቀጠም የመቀስቀሻ ዶክመንተሪ ፊልም፣ መፅሔት፣ ብሮሸር፣ ቡክሌት፣ ታዘጋጃለች/ያዘጋጃል/፡፡ ከላይ እስከታች የሚገኙ የማህበሩ አደረጃጀት እንዲያውቁት በማድረግ ተሞክሮ ከአንዱ አካባቢ ወደ አንዱ እንዲሰፉ ታደርጋለች/ያደርጋል/፡፡
  10. ሌሎች በማህበሩ የሚሰጡ ተጨማሪ ተግባራትን ያከናውናል/ታከናውናለች፡፡
Scroll to Top