ፕላን እና ፕሮግራም አስተባባሪ

ጌጡ ብርሃን

ፕላን እና ፕሮግራም አስተባባሪ

ዝርዝር የስራ ተግባራት ኃላፊነት

በአጠቃላይ ማህበሩ የሚያከናውናቸውን የተለያዩ ፕሮግራሞችን እና ፕሮጀክቶች ማስተባበር፣ በበላይነት መምራት፣ የማህበሩን ስትራቴጅካዊ ዕቅድ ማዘጋጀት፣ አፈፃፀሙን መከታተል፣ ስለፕሮጀክቶች ዝርዝር አፈፃፀም የማህበሩን አመራሮች ማማከር፣ የልዩ ልዩ ፕሮጀክት አስተባባሪ ባለሙያዎችን በበላይነት መምራት፣ መደገፍ እና ማስተባበር እንዲሁም ልዩ ልዩ አዳዲስ የፕሮጀክት ኃሳቦች በስሩ ባሉ የፕሮጀክት ባለሙያዎች እንዲመነጩ በማድረግ የሚመነጩትን ሃሳቦች በፕሮጀክትነት በማበልፅግ ሃብት ማፈላለግ እና የማህበሩን የመፈፀም አቅም በማሳደግ እና የአባላትን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ፕሮጀክቶችን የማስፈፀም ሃላፊነት ይኖረዋል፡፡

ዝርዝር ተግባራት

  1. የማህበሩን ፕሮግራሞች በበላይነት ይከታተላል፤ ይፈጽማል፤ ያስፈጽማል ያስተባብራል/ ታስተባብራለች፡፡
  2. በማህበሩ የሚፈፀሙ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ስራ ያደራጃል፣  ይከታተላል፣  በበላይነት ይመራል/ትመራለች፤
  3. የማህበሩ ስትራቴጅያዊ ዕቅድ ወቅቱን ጠብቆ እንዲዘጋጅ ያስተባብራል፣ ይደግፋል፣ በበላይነት ይመራል/ትመራለች፣
  4. የማህበሩን ስትራቴጅክ ዕቅድ፣ አመታዊ እና የግማሽ አመት እንዲሁም ሌሎች ወቅታዊ ዕቅዶችን ከሚመለከታቸው የፕሮጀክት ባለሙያዎች እና ከእቅድ ክትትል እና ግምገማ ባለሙያ ጋር በመሆን ያዘጋጃል
  5. ለማህበሩ የልዩ ልዩ የስራ ክፍል ባለሙያዎች ስለዕቀድ አስተቃቀድ፣ ክትትልና ግምገማ እንዲሁም ሪፖርት ዝግጅት ሙያዊ ክትትልና ድጋፍ ታደርጋለች/ያደርጋል፣
  6. ጽ/ቤቱ በአስቀመጠው ዕቅድ መሠረት ተግባሮቹ መፈፀም አለመፈፀማቸውን ማረጋገጥ የእቅድ አፈፃፀም ችግር /ክፍተት/ ከአጋጣመ የመፍትሔ ሃሳቦችን በማቅረብ ችግሮች እንዲፈቱ ማድረግ እቅዱ በውጤት እንዲፈፀም መስራት፡፡
  7. ልዩ ልዩ የክትትልና ግምገማ መሳሪያዎችን፣ እንዲሁም ቀልጣፋ እና አዳዲስ አሰራሮችን በማውጣት እና ከሚመለከታቸው ጋር የጋራ በማድረግ ስራ ላይ እንዲውሉ ያደርጋል/ታደርጋለች፣
  8. የማህበሩ የመደበኛ ተግባራት እና የፕሮጀክቶችን እንቅስቃሴ አጠቃላይ አፈፃፀም ያካተተ የፊዚካል ሪፖርት በየሩብ፣ በግማሽ ዓመት እና በየዓመቱ ያዘጋጃል/ታዘጋጃለች፣
  9. የፕሮግራም ሆነ የፕሮጀክቶች መደበኛ ተግባራት አፈፃፀም በማህበሩ እድገት እና አባላት ሁለንተናዊ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ላይ እያመጣ ያለውን ለውጥ፣ ፋይዳ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን እንዲገመገም ያደርጋል፣
  10. የማህበሩ አመታዊ የስራ ማስፈፀሚያ በጀት ዕቅድ በዕቅድ፣ክትትልና ግምገማ ባለሙያ እንዲዘጋጅ ታደርጋለች/ያደርጋል፣ አስፈላጊውን ሙያዊ እገዛ በማድረግ በማኔጅመንት ደረጃ የጋራ እንዲሆን ታደርጋለች/ያደርጋል፣
  11. የፕሮግራምም ሆነ የፕሮጀክት በጀት አጠቃቀሙ በዕቅዱ መሰረት እየተፈፀመ መሆኑን ይከታተላል፣
  12. የማህበሩ የመደበኛም ሆነ የልዩ ልዩ ፕሮጀክቶች ጥራት ያለው የዓመታዊ ዕቅድ እንዲዘጋጅ ያደርጋል/ታደርጋለች፣
  13. የፕሮጀክት መነሻ  ሀሳቦችን  የማመንጨትና የማዳበር ሠራ ትፈፅማለች/ይፈጽማል/
  14. ፕሮጀክቱን ለመንደፍ /ለመቅረጽ/ የሚረዱ መረጃዎችን በክልሉ  ባሉ  በአስፈላጊ   ቦታዎች  በመንቀሳቀስ ጥሬ መረጃዎችን   እንዲሰባሰቡ ያድርጋል፣  በተለያዩ   ሴክተሮች መ/ቤቶች  መንግስታዊና መንግስታዊ  ባልሆኑ ድርጅቶች በመሄድ እውነታነት ያላቸውን ሁለተኛ ደረጃ መረጃዎች እንዲሰበሰቡ በማድረግ ለሚቀረጸው ፕሮጀክት አጋዢ እንዲሆኑ ከነምንጫቸው ያስቀምጣል/ታስቀምጣለች/፡፡
  15. የተለያዩ የጥናት ፕሮፖዛሎችን ያዘጋጃል ለጥናት የሚውለው ገንዘብ  ሲገኝ  የፕሮጀክት  ጥናቱን ያካሂዳል፡፡
  16. የመጀመሪያና የሁለተኛ  ደረጃ  መረጃዎችን መሰረት በማድረግ የጽ/ቤቱን ተግባራት የሚመለከቱት ፕሮጀክቶች ማለትም እንደ ስልጠና ገቢ ማስገኛ እና ለመሳሰሉት ፕሮጀክቶች በመቅረጽና የሚቀረጹት ፕሮጀክቶች ከክልሉ አጠቃላይ መርሃ ግብር ጋር ግንኙነትና ተዛማችነት ያላቸውና  በዚያው  ዙሪያ  የተቀረጹ መሆናቸውን  በመመርመር  ተስተካክለው እንዲዘጋጁ ያስተባብራል፣ ይከታተላል/ትከታተላለች፤
  17. የፕሮጀክት ባለሙያዎችን በማስተባበር የተለያዩ ፕሮጀክቶች እንዲዘጋጁ ማድረግ፣ የተዘጋጁት ፕሮጀክቶች በሃብት እንዲደገፈ ከተለያዩ ለጋሽ ድርጅቶች ጋር  መመካከር እና ተግባራዊ እንዲደረጉ ማድረግ፣
  18. የማህበሩን የሃብት አቅም ለማሳደግ እንዲቻል የማህበሩን ልዩ ልዩ ገቢ በተሻለ መንገድ ለመጠቀም የሚያስችሉ የአሰራር ስልቶች እንዲቀየሱ እና ተግባራዊ እንዲሆኑ ከማህበሩ አመራሮች ጋር በጋራ ይሰራል/ትሰራለች፣
  19. የማህበሩን የገቢ አቅም እና የአባላት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንዲቻል ማህበሩ ከልዩ ልዩ ለጋሽ ድርጅቶች ጋር ያለው አጋርነት እና ቅንጅታዊ አሰራር እንዲጠነክር ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል፣ ማህበሩንም በመወከል በልዩ ልዩ የፕሮጀክት አጋርነት ስብሰባዎች ላይ በመገኘት የአጋርነት እና ቅንጅታዊ አሰራር እንዲጎለብት ይሰራል/ትሰራለች፤
  20. በማህበሩ የሚተገበሩ ፕሮጀክቶች በዕቅዱ መሰረት ወቅቱን ጠብቀው እንዲፈፀሙ እና ለተባለለት ኣላማ እንዲውል ለፕሮጀክት ባለሙያዎች አስፈላጊውን ክትትልና ድጋፍ ያደርጋል፣ የፕሮጀክቱን አፈፃፀም ይከታተላል፣ በኘሮጀክቱ እቅድ መሠረት በየደረጃው በሚገኙ አደረጃጀቶች ተግባሮች መፈፀማቸውን መከታተል ያመጡትን ተጨባጭ ውጤት መለካት የገጠሙ ችግሮችን በመለየት መፍታትና ለሚመለከተው ኃላፊ ማሣወቅ፣
  21. በስሩ/ሯ ላሉ ባለሙያዎች ወቅቱን የጠበቀ የስራ ቸክሊስት እያዘጋጀ ይሰጣል፣ የስራ አፈፃሙን መሰረት ያደረገ ውጤት ይሰጣል/ትሰጣለች፣
  22. በማህበሩ የሚተገበሩ ልዩ ልዩ ፕሮጀክቶችን በጀት በአግባቡ ስራ ላይ እንዲውል ይመራል ይከታተላል/ትከታተላለች
  23. በእያንዳንዱ ፕሮጀክት ስራ ክፍል እንደ ፕሮጀክቱ የስራ ባህሪ የፕሮጀክቱን ዶክመንትና የፋይናንስ ዳታውን በ15ቀን፣ በወር፣ በሩብ አመት እና በዓመት እንዲዘጋጅ በማድረግ፣ ለማህበሩ ዳይሬክተር/ም/ዳይሬክትር እና ለዶነሮች ሪፖርት  ያደርጋል/ታደርጋለች/፡፡
  24. የሚፈፀሙ ተግባራትን በ15 ቀን፣ በወር፣ በሩብ አመት እና በዓመት እየታቀዱ እንዲፈፀሙ፣ ከሁሉም የፕሮጀክት ባለሙያዎች እና የክትትልና ግምገማ ባለሙያ ወቅቱን የጠበቀ ሪፖርት እንዲዘጋጅ ክትትልና ድጋፍ ያደርጋል/ታደርጋለች፣ በተመሳሳይ በተገለፁት ጊዜያት ለኃላፊ ሪፖርት ታደርጋለች /ያደርጋል/፣
  25. በማህበሩ የሚተገበሩ ልዩ ልዩ ፕሮጀክቶችን ከሚኖረው የስራ መደራረብ እና የስራ ቀረቤታ ጋር ታሳቢ በማድረግ ለፕሮጀክት ባለሙያዎች አስተዳደራዊ በሆነ መልኩ ስራ ክፍፍል ይሰጣል፣
  26. ሌሎች በጽህፈት ቤቱ የሚሰጡትን/የሚሰጧትን ተግባራት ያከናውናል፡፡
  27. የማህበሩን የመደበኛ እና የፕሮጀክት እቅዶችን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን እና በተነጣል ያዘጋጃል/ታዘጋጃለች፤
  28. የማህበሩ ስትራቴጅያዊ ዕቅድ ወቅቱን ጠብቆ ያዘጋጃል/ታዘጋጃለች፣ ይደግፋል፣ በበላይነት ይመራል/ትመራለች፣
  29. የማህበሩን ስትራቴጅክ ዕቅድ፣ አመታዊ እና የግማሽ አመት እንዲሁም ሌሎች ወቅታዊ ዕቅዶችን ከሚመለከታቸው የፕሮጀክት ባለሙያዎች ጋር በመሆን ያዘጋጃል
  30. ለማህበሩ የልዩ ልዩ የስራ ክፍል ባለሙያዎች ስለዕቀድ አስተቃቀድ፣ ክትትልና ግምገማ እንዲሁም ሪፖርት ዝግጅት ሙያዊ ክትትልና ድጋፍ ታደርጋለች/ያደርጋል፣
  31. ጽ/ቤቱ በአስቀመጠው ዕቅድ መሠረት ተግባሮቹ መፈፀም አለመፈፀማቸውን ማረጋገጥ የእቅድ አፈፃፀም ችግር /ክፍተት/ ከአጋጣመ የመፍትሔ ሃሳቦችን በማቅረብ ችግሮች እንዲፈቱ ማድረግ እቅዱ በውጤት እንዲፈፀም መስራት፡፡
  32. ልዩ ልዩ የክትትልና ግምገማ መሳሪያዎችን፣ እንዲሁም ቀልጣፋ እና አዳዲስ አሰራሮችን በማውጣት እና ከሚመለከታቸው ጋር የጋራ በማድረግ ስራ ላይ እንዲውሉ ያደርጋል/ታደርጋለች፣
  33. የማህበሩ የመደበኛ ተግባራት እና የፕሮጀክቶችን እንቅስቃሴ አጠቃላይ አፈፃፀም ያካተተ የፊዚካል ሪፖርት በየሩብ፣ በግማሽ ዓመት እና በየዓመቱ ያዘጋጃል/ታዘጋጃለች፣
  34. የፕሮግራም ሆነ የፕሮጀክቶች መደበኛ ተግባራት አፈፃፀም በማህበሩ እድገት እና አባላት ሁለንተናዊ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ላይ እያመጣ ያለውን ለውጥ፣ ፋይዳ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን እንዲገመገም ያደርጋል/ታደርጋለች፣
  35. የማህበሩ አመታዊ የስራ ማስፈፀሚያ በጀት ዕቅድ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በጋራ ያዘጋጃል፤
  36. የፕሮግራምም ሆነ የፕሮጀክት በጀት አጠቃቀሙ በዕቅዱ መሰረት እየተፈፀመ መሆኑን ይከታተላል፣
  37. የማህበሩን ዓላማዎች መሠረት በማድረግ በየደረጃው በተለያዩ የቅስቀሳ መድረኮች እንዲዘጋጁ ስልቶችን ይነድፍል፣ የመደራጀት ጠቀሜታን አመራሩ አጠቃላይ ሴቶች እንዲያውቁ ለማድረግ ትንቀሳቀሳለች/ይንቀሳቀሳል/፡፡
  38. የሚፈፀሙ ተግባራትን በ15 ቀን፣ በወር፣ በሩብ አመት እና በዓመት እያቀዱ በመፈፀም በተመሳሳይ በተገለፁት ጊዜያት ለኃላፊ ሪፖርት ታደርጋለች /ያደርጋል/፡፡
  39. በተጨማሪ ከኃላፊ የሚሰጡትን ስራዎች ያከናውናል/ታከናውናለች/፡፡

 

 

Scroll to Top