የአስተዳደር እና ፋይናንስ ክፍል ኃላፊ (Administration& Finance Head) ዝርዝር የስራ ተግባራት ኃላፊነት

ወ/ሮ አበቡ መከተ
የአስተዳደር እና ፋይናንስ ክፍል ኃላፊ
የአስተዳደር እና ፋይናንስ ክፍል ኃላፊ (Administration& Finance Head)
ዝርዝር የስራ ተግባራት ኃላፊነት
- በፋይናንስ ደንብ መሰረት ለማህበሩ የተመደበውን መደበኛ በጀት ይቆጣጠራል ይመዘግባል፣ ያመዛዝናል፡፡
- ተከታታይነት ባለው መንገድ የማህበሩ ገቢ እና ወጭ እንቅስቃሴ (Cash flow) እንዲዘጋጅ ያደርጋል፣ አፈፃፀሙንም ይከታተላል/ትከታተላለች፡፡
- የገቢ ወጭ ሰነዶችን ቅጾች ሞዴሎችና ቫውቸሮች ለውጭም ሆነ ለውስጥ ኦዲተሮች ቁጥጥር በማንኛው ጊዜ አመቺ ሆነው እንዲቀመጡ ያደርጋል፡፡
- የገቢና ወጭ ሞዴሎች የተለያዩ ሰነዶች ደረሰኞች ሌሎች አባሪ ማስረጃዎች ከወጭ ማመሳከሪያው ጋር በጥንቃቄ እንዲያዙ አድርጎ ያረጋግጣል፡፡
- የወጪ ሰነዶች ትክክልለኛነታቸውን ያረጋግጣል ክፍያዎችን ያፀድቃል፡፡
- በየወጭ እርስ የተፈቀደውን በጀት በየእርሳቸው አጣጥሞ ለመስራት ጥረት ያደርጋል፣ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ የበጀት ዝውውር ያደርጋል፣ አፈጻጸሙን ይከታተላል፡፡
- ያልተወራረዱ እና በእንጥልጥል ላይ ያሉ ሰነዶች እንዲወራረዱ መግለጫ ያቀርባል አፈጻፀሙን ይከታተላል ፡
- የዞኖች ሂሳብ ወቅቱን ጠብቆ እንዲወራረድ ክትትልና ድጋፍ ያደርጋል፡፡
- የፕሮጀክቶችን ሂሳብ ይከታተላል ችግር ካለ ለሃላፊው ያሳውቃል፡፡
- በየወሩ የሳጥን የሂሳብ ሚዛን ይሰራል፣ ያረጋግጣል ይከታተላል የመደበኛና የኘሮጀክት ሂሳብ በወቅቱ እንዲመዘገብ ያደርጋል፡፡
- በማህበሩ የስራ እቅድና በጀት ዝግጅት ስራ ላይ ይሳተፋል በበጀት እቅድም በአመቱ መጀመሪያ ያዘጋጃል፡፡
- እንደማህበሩ ሥራ ክብደትና ቅለት በካዝና ማደር የሚገባውን የጥሬ ገንዘብ መጠን ለማሻሻል ከሃላፊዎች ጋር በመመካከር ያሻሽላል፡፡
- ሁሉንም የሂሳብ አካውንት መምራትና መቆጣጠር፡፡
- የደመወዝ ክፍያ ትክክለኛነት ያረጋግጣል፡፡
- የባንክ ማስታረቂያ በየወሩ እንዲሰራ በማድረግ የማህበሩን የባንክ እንቅስቃሴ ይቆጣጠራል ፡፡
- የማህበሩንም ሆነ የፕሮጀክት ገንዘብ ብክነት (ጉድለት) እንዳይደርስበት ይቆጣጠራል/ ትቆጣጠራለች፡፡
- እዳ ያለበትን ሠራተኛ ቢለቅ የማህበሩን ገንዘብ ሣይመልስ መልቀቂያና ጥቅማጥቅም እንዳይሰጠው ያደርጋል/ታደርጋለች፡፡
- በባንክ እና በሳጥን ያለ ገንዘብ ሚዛን ከሌጀር ጋር እኩል መሆኑን ይቆጣጠራል፡፡
- አስፈላጊው የግዥ ዝርዝር ጥያቄ ወቅቱን ተብቆ እንዲቀርብ ደርጋል/ታደርጋለች፣ የግዥ ትዕዛዝ ሲቀርብ በአርስቱ በጀት መኖሩን ይቆጣጠራል፣ በቀረበው የግዥ ጥያቄ መሰረት አስፈላጊው ግዥ ወቅቱን ጠብቆ እንዲፈፀም ይከታተላል፣ ያስተባብራል/ታስተባብራለች፡፡
- በአመቱ መጨረሻ የሳጥን፣ የገንዘብ ሰነድ ቆጠራ ያደርጋል፡፡
- በየወሩ የማህበሩን የፋይናንስ ሪፖርት አዘጋጅቶ ለተቋሙ ሃላፊ ያቀርባል፡፡
- የፕሮጀክቶችን እና የማህበሩን የመደበኛ የሂሳብ እንቅስቃሴ ከፕሮግራም ማናጀሩ ጋር በመናበብ እና በመመካከር ለሃላፊ ያቀርባል/ታቀርባለች፡፡
- የፕሮጀክቶች የስራ እንቅስቃሴ ሪፖርት በየወሩ፣ ሩብ ዓመቱ፣ ግማሽ አመቱ እና በየዓመቱ በጥራት ተሰርቶ ለሚመለከተው የፕሮጀክት አስተባባሪ፣ የክትትልና ግምገማ ባለሙያ፣ ለኃላፊ እና ለፕሮጀክት ጽ/ቤት እንዲላክ ያደርጋል፡፡
- በበጀት አመቱ መጨረሻ ላይ የአመቱን በጀት ዘገባ ያዘጋጃል፡፡
- የማህበሩ ዕዳ የሆኑትን በመለየት በወቅቱ ለሚመለከተው አካል እንዲከፈል ያደርጋል፡፡
- ወቅቱን ጠብቆ ከዞን እስከ ቀበሌ ድረስ ደመወዝና ሥራ ማስኬጀ በባንክ እንዲላክ ያደርጋል፡፡
- ከማህበሩ ውጭ የሚሰሩ ኘሮጀክቶችን ሰነድ ፌደራል በሚጠይቅበት ሰዓት የወጪ ሰነዶችን እንዲወራረድ ያደርጋል፡
- የአባላት መዋጮ ገቢን በባንክ ማስረጃ በማምጣት ገቢው እንዲመዘገብ ያደርጋል፡፡
- የማህበሩ ቋሚ እቃ አመታዊ የእርጅና ቅናሽ እየተሰላ እንዲመዘገብ ያደርጋል፡፡
- ከማህበሩ ሊቀ መንበር እና የፅ/ቤት ኃላፊ ጋር በጋራ በጣምራ ፊርማ ቸክ ይፈርማል፡፡
- በስሩ ያሉትን ባለሙያዎች (የሂሳብ ባለሙያ፣ የሰው ኃይል እና አስተዳደር፣ የጽዳት፣ ተላላኪ እና ፎቶ ኮፒ ግዥ ባለሙያ፣ ገንዘብ ያዥ እና ንብረት ክፍል ሹፌር፣ ጥበቃ፣ ) አስፈላጊውን ክትትልና ድጋፍ ያደርጋል፣ አፈፃፀማቸውን ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፡፡
- በስሩ ያሉትን ሰራተኞች የ6 ወር ስራ አፈፃፀም ውጤት ይሞላል፡፡
- ልዩ ልዩ የሰው ኃይል አስተዳደር ስራዎች ወቅቱን ጠብቆ እየተፈፀሙ መሆናቸውን ክትትልና ድጋፍ ያደርጋል፣ ስራው በአግባቡ መፈፀሙን በበላይነት ይቆጣጠራል፡፡
- የማህበሩ የአጠቃላይ የሂሳብ እንቅስቃሴ በየበጀት ዓመቱ ማጠቃለያ በውጭ ኦዲተር ኦዲት እንዲደረግ እና የኦዲት ሪፖርቱ ለመሚመለከታቸው አካላት እንዲላክ ያደርጋል፡፡
- በኦዲተሮች የሚሰጡ አስተያዮቶች ፈጥነው እንዲስተካከሉ እና በማህበሩ ምንም አይነት የፋይናንስ እና አስተዳደር ብልሹ አሰራር እንዳይኖር ይከታተላል፡፡
- ከኃላፊው የሚሰጡትን ሌሎች ተመሳሳይ ተግባራት ያከናውናል/ታከናውናለች/፡፡
