ለሚዲያ ባለሙያወች ስልጠና ተሰጠ።
የአማራ ሴቶች ማህበር ከተባበሩት መንግስታት የስነ ህዝብ ፈንድ /UNFPA/ ጋር በመተባበር ለጋዜጠኞች ለህዝብ ግንኙነትና ኮምንኬሽን ባለሙያዎች ፆታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች አዘጋገብና ሪፖርት አዘገጃጀት ትኩረት ያደረገ ስልጠና ሚያዚያ 07/2016ዓ.ም በባህርዳር ከተማ ስልጠና እየተሰጠ ነው።
በስልጠናው የማህበሩ የቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሮ ዳርእስከዳር ጌቴ ተገኝተው በመክፈቻ ንግግራቸው ስለማህበሩ አጠር ያለ ማብራሪያ ከሰጡ በኋላ ባስተላለፉት መልዕክት የሚዲያ ባለሙያወች ፃታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች መከላከልና ምላሽ መስጠት ላይ ማስገንዘብ መሳወቅ ይጠበቅባቸዋል ማህበረሰባችንም የጥቃቶችን መንስኤዎችና የሚያስከትሉትን ችግሮች ላይ ግንዛቤው አናሳ በመሆኑ የሚዲያ ባለሙያወች በዘገባቸው የማህበረሰብን አስተሳሰብ የመቀየር አቅም ስላላቸው ትኩረት አድርገው እንዲሰሩ ያለመ ስልጠና ነው ብለዋል።
ስልጠናው ለሶስት ተከታታይ ቀናት ይቀጥላል።