
የአማራ ሴቶቾ ማህበር 1.3 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ።
ማህበሩ ከተባበሩት መንግስታት የስነ-ህዝብ ፈንድ/UNFPA/ ጋር በመተባበር በ5 ዞኖች ፆታን መሰረት ያደረገ ጥቃት መከላከልና ምለሽ መስጠት ፕሮጀክት እንደሚተገበር ይታወሳል።
ይኽ ፕሮጀክት የ2024እ. ኤ. አ የመጀመሪያ ሩብ አመት የስራ ግምገማ ጠቅላላ ሰራተኛው ጋር አድርጓል።
ፕሮጀክቱ በሩብ አመቱ ለ40የፊስቱላ ታካሚዎች 419,000 ብር ለፆታዊ ጥቃት ተጋላጭ ሴቶች የቀጥታ ገንዘብ ድጋፍ 948,000 ብር በድምሩ 1,367,000 ብር ድጋፍ አድርጓል።ለሴቶች ማረፊያ ክፍል የእቃ አቅርቦት ግዥ ከመደረጉ በተጨማሪ የስነ ልቦና ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው 342 የህብረተሰብ ክፍሎች የማማከር ስራና በየቀበሌው የማህበረሰብ ውይይት ማድረጉን በሪፓርቱ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።
በተጨማሪም የማህበሩ ጠቅላላ ሰራተኛ የመደበኛና የፕሮጀክት ተግባራትን እስከ ሰኔ 30 ተሰርቶ የሚጠናቀቅ የቀሪ ወራት ስራዎችን በመከፋፈል ውይይቱን አጠናቋል።