
የአማራ ሴቶች ማህበር በ4ኛው ዙር 5.9 ሚሊዮን ብር ለኤች አይቪ ኤዲስ ተጋላጭ ለሆኑ ሴቶች ከወለድ ነፃ ተዘዋዋሪ ብድር ማሰራጨቱን አሳወቀ፡፡
ማህበሩ ከዚህ ቀደም በአማራ ክልል
በሁሉም ዞኖች በ52 ከተማና ወረዳ አስተዳደሮች በ3 ዙር 12045 ሴቶችን ተጠቃሚ ማድረጉ የሚታዎስ ነው፡፡
በዚህ ስድስት ወር ደግሞ ለ326ሴቶች 5‚950‚000 ሚሊዮን ብር ለእያንዳንዳቸው 20‚000 መስጠቱን የገለፁት የግሎባል ፈንድ አስተባባሪ ወ/ሮ በላይነሽ ሽባባው ናቸው፡፡
አስተባባሪዋ አክለውም ሴቶቹ ይህንን ብድር በመውሰዳቸው ቤት ንብረት ያፈሩ ካፒታላቸውን 400‚000 ብር ድረስ በማድረስና ልጆቻቸውን በማስተማር ለቁም ነገር አድርሰው ኑሮዋቸውን እየኖሩ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡