የአማራ ሴቶች ማህበር የምዕራብ አማራ ዞኖችና ከተማ አስተዳደሮች ጋር የ2016ዓ.ም እቅድ አፈፃፀም ሪፓርት ግምገማዊ ውይይትና የ2017ዓ.ም እቅድ ትውዉቅ መስከረም 20/2017ዓ.ም በባህር ዳር ከተማ አካሄደ።
የ2016ዓ.ም ሪፓርት በማህበሩ ም/ዳይሬክተር ወ/ሮ ሁሉአየሽ አወቀ የቀረበ ሲሆን የ2017ዓ.ም እቅድ ደግሞ በፕላንና ፕሮግራም ባለሙያው አቶ ጌጡ ብርሀን ቀርባል።
በዉይይቱ የማህበሩ የቦርድ ፀሀፊ ወ/ሮ ማህሌት ጥላሁን ባስተላለፉት መልዕክት የ2016ዓ.ም የተሻለ ስራ ለመስራት ምቹ ሁኔታ ባይኖርም በተቻለው አጋጣሚ ሁሉ ስራዎችን ለማከናወን የተደረገውን ጥረት አበረታትተዋል።
ባሳለፍነው ሳምንት በደሴ ከተማ የምስራቅ አማራ ሴቶች ማህበር ግምገማዊ ውይይት መደረጉ ይታወሳል በዚህም ደቡብ ወሎ ፣ ኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን እንዲሁም ሰሜን ጎንደር ዞን በዞን ደረጃ በወጣው መስፈርት ከአንድ እስከ ሶስት ደረጃ ወጥተዋል።ዋግኸምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ደግሞ 4ኛ ወጥቷል።
ከከተማ አስተዳደሮች ደግሞ ደብረብርሀን፣ጎንደርና ደሴ ከተሞች ደረጃቸው ይፋ መደረጉና ሽልማታቸውን መውሰዳቸው የሚታወስ ነው።
በፕሮግራሙ የጎንደር ከተማ አስተዳደር ሁለተኛ ደረጃ በመውጣት የዲስክ ቶፕ ኮምፒውተር ተሸላሚ ሁኗል።
በመጨረሻም የማህበሩ የቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሮ ዳርእስከዳር ጌቴ የስራ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
አደረጃጀቱንና አሰራሮችን ማጠናከር፤ ሁሉም ዞኖች በየደረጃው እቅድ ኦሬንቴሽን እንዲሰጡ፤ቅንጅታዊ አሰራሮችን እንዲጠናከር፤ከወለድ ነፃ ተዘዋዋሪ ተበዳሪዎችንና የልዬ ልዬ ሀብት መረጃዎችን መያዝ፤የህዝብ ግንኙነት ስራችን አጠናክሮ መያዝ፤ተንጠልጣይ ሰነዶችን የማወራረድና የአባላት ክፍያ ትኩረት ተደርጎባቸው እንዲሰሩ አቅጣጫ አስቀምጠዋል