የ333,991$ ፕሮጀክት ይፋዊ ስምምነት ተደረገ።

የ333,991$ ፕሮጀክት ይፋዊ ስምምነት ተደረገ።

የአማራ ሴቶች ማህበር ከተባበሩት መንግስታት የህፃናት መርጃ ድርጅት/UNICEF/ ጋር በመተባበር ስርአተ ፆታን መሰረት ያደረገ ጥቃት መከላከልና ምላሽ መስጠት ፕሮጀክት ለመተግበር ስምምነት ወስዷል።

ፕሮጀክቱ በምዕራብና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች ውስጥ ሞጣ፣ወንበርማ፣ደጀንና ሰከላ ወረዳዎች ይተገበራል።

ህዳር 26/2018ዓ.ም በባህርዳር ከተማ የፕሮጀክት ትውውቅ በተደረገበት መድረክ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የማህበሩ የቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሮ ዳር እስከዳር ጌቴ ማህበሩ ፕሮጀክትን የመፈፀምና የማስፈፀም አቅም በማዳበሩ እንዲሁም ተግባራትን በትብብር የመስራት ባህልን በማዳበሩ ስራዎች በታቀደላቸው የጊዜ ገደብ እየተጠናቀቁ እንዳሉ ገልፀው የፕሮጀክት ሰራተኞች የማህበሩን የስራ ባህል በመጠበቅ ተግባራትን ከመደበኛ ስራ ጋር እያቀናጁ መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።

በተጨማሪም ከማህበረሰቡ የግንዛቤ እጥረት ምክንያት እየተከሰተ ያለውን ስርአተ ፆታን መሰረት ያደረገ ጥቃት ከጊዜ ጊዚ እየጨመረ በመምጣቱ ይሄንን ተግባር ለመከላከልና ምላሽ ለመስጠት ፕሮጀክቱ አጋዥ ነው ብለዋል።

የማህበሩ ዳይሬክተር ወ/ሮ ገነት ወንድም በበኩላቸው ፕሮጀክቱ ወደ ማህበሩ እንዲመጣ አስተዋፅኦ ያበረከቱ UNICEF እና የማህበሩን የሀብት አፈላላጊ ኮሚቴዎችን አመስግነዋል አያይዘውም የወረዳ ባለሙያዎች ተግባራትን ሲከውኑ ከመደበኛ ስራው ጋር በቅንጅት መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top