የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ምላሽ ለመስጠት ሀብቶችን በአግባቡ መያዝ እንደሚገባ ተጠቆመ።
የአማራ ሴቶች ማህበር የቦርድ አመራሮች የ2018ዓ.ም በጀት አመት የአንደኛው ሩብ አመት የአፈፃፀም ግምገማ ህዳር 20/2018ዓ.ም በባህርዳር ከተማ አካሂዷል።
የፅህፈት ቤቱን የሩብ አመት አፈፃፀም ያቀረቡት የማህበሩ ም/ዳይሬክተር ወ/ሮ ሁሉአየሽ አወቀ የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ ማህበራዊ ጥቅሞቻቸውን ከማስከበር አኳያና እየደረሱ ያሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ከመፍታት አኳያ ዘርዘር ያለ ሪፖርት አቅርበዋል።
በውይይቱም ማህበሩ እፈፅማለሁ ብሎ ካቀዳቸው እቅዶች አኳያ ከጊዜ ጊዜ አሰራሮች እየተሻሻሉ መምጣታቸው ተግባብቶና ተቀናጅቶ ከመስራት የመጣ ነው ተብሏል።
የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ምላሽ ከሚሰጥባቸው ተግባሮች አንዱ በየዞኑ ያሉ የማህበሩ ልዮልዮ ሀብቶችን ከብልሹ አሰራር በመጠበቅና በአግባቡ በማስተዳደር ለታለመለት አላማ እንዲውል በርብርብ መሰራት እንደሚገባም ተጠቁሟል።
የማህበሩን መሰረት በማስፋት የተሻለ አስተሳሰብና አሰራር ስርአት ለመዘርጋት ሴት ሙሁራንን ወደ ማህበሩ ለማቀላቀል እየተሰራ ያለው ስራ አበረታች እንደሆነም ተጠቁሟል።
በመጨረሻም የተሻለ አሰራሮችን ማስቀጠል ደካማ አፈፃፀሞችን ደግሞ ማረም እንደሚገባና የተለያዩ የስራ አቅጣጫውን በማስቀመጥ ውይይቱ ተጠናቋል።



