
ተቋማዊ የጥንካሬና ድክመት ዳሰሳዊ ጥናት ተደረገ።
ከአማራ ሴቶች ማህበር ጋር በመተባበር ስርአተ ፆታን መሰረት ያደረገ ጥቃት ለመከላከልና ምላሽ ለመስጠት የቅድመ ዝገጅት ስራ እየሰራ የሚገኘው Norwegian church aid የማህበሩን የጥንካሬና የድክመት የዳሰሳ ጥናት ከህዳር 16-18/2018ዓ.ም አካሂዷል።በሂደቱም በተቋሙ ዳይሬክተር ወ/ሮ ገነት ወንድሙ በሚመራው የሀብት አፈላላጊ ቡድን ጋር ጥልቅ ውይይት አድርገዋል ማህበሩ ያለው ተቋማዊ አሰራርና መዋቅራዊ አደረጃጀቱ ለስራ ምቹ እንደሆነና በትብብር ለመስራት አመች ሁኔታን እንደሚፈጥር አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
