በአማራ ሴቶች ማህበር በጎንደር ከተማ ሲስጥ የነበረው የሴት ምክር ቤት አባላት የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ተጠናቀቀ፤

ታህሳስ/2018 ዓ/ም የአማራ ሴቶች ማህበር ከሄልቬታስ ኢትዮጽያ ALGP በተገኘ የበጀት ድጋፍ እና አሰተባባሪነት ለጎንደር ከተማ ምክር ቤት ለሴት የምክር ቤት አባላት ለሁለት ቀን በተለያዩ ርዕሶስ ጉዳዮች የምክር ቤቶች የአሰራር ስርዓት መመሪያ፤ የመሪነት ጽንሰ ሃሳብ፤ የንግግር ክህሎት ማመቻቸትና ማስተማር በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ሲሰጥ የነበረው የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ተጠናቋል።

የምክር ቤቱ ምክትል አፈጉባኤ የሆኑት የተከበሩ አቶ ስለሺ መስፍን እንዳሉት በተሰጠው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስለጠና ሴቶች የመናገር ክህሎታቸውን በማዳበር ያሉ ችግሮችን በራሳቸው የመፍታት አቅማቸው ከማጠናከር በተጨማሪ በተዋረድ የቀበሌ ምክር ቤት ሴት ፎረም አባላትንና የአማራ ሴቶች ማህበር ላይ በመደገፍ የተሻለ ማህበረሰብ እንዲፈጠር መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።

ሰልጣኞች(የሴት ፎረም አባላት)እንደገለጹት የተሰጠው ስልጠና አቅማችን ይበልጥ የሚያጎለብትና ለቀጣይ የበለጠ እንድንጠናከር የሚያግዝ ነው ብለዋል፡፡

መረጃው፦የጎንደር ከተማ ምክር ቤት

ህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ነው

ታህሳስ/2018ዓ.ም

ጎንደር//

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top