ማህበሩ የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር በመተባበር ይሰራል።የደብረ ብርሀን ከተማ አስተዳደር የአማራ ሴቶች ማህበር ወፈል የበጎ አድራጎት ማህበር ጋር በመተባበር በተለያዩ ምክንያቶች ተፈናቅለው ለመጡና ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ውስጥ ለሚገኙ አምስት ሴቶችን በማደራጀት 250,000 ብር የመነሻ ካፒታል በመስጠትና የገበያ ትስስር ተፈጥሮላቸው ወደስራ እንዲሰማሩ ተደርጓል።



