የአማራ ሴቶች ማህበር እና ኖርዌዥያን ቸርች ኤድ ስርአተ-ፆታን መሰረት ያደረገ ጥቃትን በመከላከል ዙሪያ ተወያዩ።

​የአማራ ሴቶች ማህበር እና የኖርዌዥያን ፒፕል ኤድ (Norwegian people’s Aid) የስራ ቡድን ስርአተ-ፆታን መሰረት ያደረገ ጥቃትን መከላከልና ምላሽ መስጠት ተግባራት ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችል ውይይት አካሄዱ።

​የኖርዌዥያን ፒፕል ኤድ ቡድን ከማህበሩ የሀብት አፈላላጊ ኮሚቴ ጋር ባደረገው ውይይት፣ ማህበሩ በጥቃት መከላከልና ምላሽ መስጠት ረገድ ያለበትን የስራ ደረጃ ለመገምገም እና በቀጣይ በትብብር ለመስራት ያለውን ሁኔታ ለማወቅ ውይይት አድርጓል።

​በማህበሩ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ገነት ወንድሙ በሚመራው የሀብት አፈላላጊ ቡድን ጋር በተደረገው ጥልቅ ውይይት፣ የማህበሩ ተቋማዊ አሰራር እና መዋቅራዊ አደረጃጀት ለወደፊት የጋራ ስራዎች አመቺ መሆኑን የኖርዌጂያን ፒፕል ኤድ የስራ ቡድን አባላት ገልጸዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top