ሴቶች ማህበር በተዘዋዋሪ ብድር  የሴቶችን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት እያረጋገጠ መሆኑን ገለጸ።

ባህር ዳር — መጋቢት 29/2018 ዓ.ም

የአማራ ሴቶች ማህበር የግሎባል ፈንድ (Global Fund) ተዘዋዋሪ ብድር የዘጠኝ ወር እቅድ አፈጻጸም ሪፖርትን ከስትሪንግና ቴክኒክ ኮሚቴዎች ጋር በጋራ በመሆን ገመገመ።

በግምገማ መድረኩ ላይ የተገኙት የማህበሩ የቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሮ ዳር እስከዳር ጌቴ እንደገለጹት፤ ማህበሩ ከአጋር አካላት ጋር በመቀናጀት በሴቶች ላይ የሚደርሱ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ  ጫናዎችን ለመቀነስ በትኩረት እየሰራ እንደሆን ተናግረዋል  በተለይም ተጋላጭ ሴቶችና ልጃገረዶችን ከወለድ ነፃ በሆነ ብድር በመደገፍ፣ የኢኮኖሚ አቅማቸውን ለማሳደግና ማህበራዊ ችግሮቻቸውን ለመፍታት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

ይህ የግሎባል ፈንድ ፕሮጀክት በሁሉም ዞኖችና በ52 የከተማ አስተዳደሮች የሚገኙ ሴቶችን ከጥገኝነት ነፃ የሚያደርጉ ተግባራትን ሲያከናውን የቆየ ሲሆን፤ ሴቶች በኢኮኖሚ ራሳቸውን እንዲችሉ በማድረግ ለኤች.አይ.ቪ/ኤድስ (HIV/AIDS) ተጋላጭነታቸውን በመቀነስ ረገድ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ መሆኑ አመላክተዋል።

የአብክመ የሴቶችና ወጣቶች ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ም/ሀላፊ የሆኑት ወ/ሮ ዝና ጌታቸው በበኩላቸው  ማኅበሩ ከሚፈፅመው ፕሮግራም መልካም ተሞክሮ የሚወሰደው ተዘዋዋሪ ብድር ፈንድ ለሌሎች  ሥራዎቻችን እንደ አርአያ የሚጠቀስ የብድር ሥርዓት መዘርጋት መቻሉ ነው ብለዋል። ይህ አሠራር በርካታ ሴቶችን ከኢኮኖሚ ችግር በማውጣትና የራሳቸው ሀብትና ንብረት ባለቤት በማድረግ ረገድ ከፍተኛ ለውጥ አምጥቷል። በመሆኑም የድጋፍና የክትትል ሥርዓቱ  በማጠናከርና ተግባራትን በየጊዜው እየገመገሙ በመምራት  ዋነኛ ተግባር ተደርጎ ሊወሰድ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

 [4/8/2026 4:56 AM] Amhara women association .AWA: የአብክመ ጤና ቢሮ  HIV/ADIS ዘርፈ ብዙ ምላሽ ማስፋትና ማጠናከር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ውድነህ ገረመ የድጋፍና ክትትል ስርአቱን በማጠናከር ተጠቃሚዎች ያመጡት ተጨባጭ ለውጥ በየጊዜው እየተመዘገበ የሪፖርት አካል ሆኖ መገምገም እንዳለበት አመላክተዋል።

የማህበሩ የተዘዋዋሪ ብድር  ግሎባል ፈንድ ፕሮጀክት አስተባባሪ ወ/ሮ በላይነሽ ሽባባው በሪፖርታቸው እንደገለጹት በዘጠኝ ወር ውስጥ ለ349 ሴቶች 7 ሚሊዮን ብር ከወለድ ነፃ ተዘዋዋሪ ብድር መሰራጨቱንና ሴቶቹ ተጨባጭ ለውጥ በማምጠት ከተጋላጭነት እራሳቸውን እያወጡ የሀብት ንብረት ባለቤት እየሆኑ እንደሆነ በሪፖርታቸው አንስተዋል፡፡

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top