የአማራ ሴቶች ማህበር እና ሄልቬታስ ኢትዮጵያ በመቀናጀት በማህበረሰብ አሳታፊ እቅድ የአካባቢያዊ አስተዳደር ፕሮጀክት በርካታ ተግባራን አከናወኑ፡፡

የአማራ ሴቶች ማህበር ከሄልቬታስ ኢትዮጵያ ጋር በመተባባር የአማራ አካባቢያዊ አስተዳደር ፕሮጀክት (Amhara Local Governance Project Plus – ALGP+) ፕሮጀክትን በጎንደር ዙሪያ፣ በላይ አርማጭሆ ወረዳዎች እና በጎንደር ከተማ አስተዳደር ሲተገብር የቆየው ዘላቂ ልማትን የማረጋገጥና ድህነትን የመቀነስ ንቅናቄ ተጨባጭ ለውጦችን በማስመዝገብ ላይ ይገኛል።

ይህ ፕሮጀክት በሶስት አመት ቆይታው በዋናነት የማህበረሰቡን አቅም በልማት ዕቅድ አስተዳደር ዙሪያ ማሳደግ እና የምክር ቤቶችን አሠራር ማጠናከር ላይ ትኩረት አድርጎ የቆየ ሲሆን፣ ማህበረሰቡ በእያንዳንዱ የልማት ሂደት ውስጥ የባለቤትነት ስሜት ኖሮት ንቁ ተሳታፊ እንዲሆን አስችሏል።

በወረዳና በቀበሌ ደረጃ “የተቀናጀ ማህበረሰብ አቀፍ አሳታፊ ዕቅድ” ተግባራዊ በማድረግ፣ የሕዝቡ ፍላጎት በቀጥታ በልማት ዕቅዶች ውስጥ እንዲካተት ተደርጓል። የምክር ቤቶች አሠራርም ይበልጥ እንዲጠናከር ተደርጓል።

በገጠር መሠረተ ልማት መስፋፋት፣ በተፈጥሮ ሀብት አያያዝ የማህበረሰቡን የዕለት ተዕለት ሕይወትና ትስስር አሻሽሏል።

ወቅታዊና አስገዳጅ በሆኑ ሁኔታዎች ላይ ፈጣንና ውጤታማ የአስቸኳይ ጊዜ ምላሽ ተግባራትን በማከናወን ረገድ ፕሮጀክቱ ግንባር ቀደም ሚና ተጫውቷል።

“የተቀናጀ ማህበረሰብ አቀፍ አሳታፊ ዕቅድ” ማህበረሰቡንና መንግስትን በማስተባበር በየአካባቢው በርካታ ስራዎች ተሰርተዋል የውሀ ማፋሰሳሻ የንፁህ መጠጥ ውሀ ግንባታ የት/ቤቶች ግንባታ ስራዎች ተከናውነዋል፡፡

የአማራ ሴቶች ማህበር ከተለያዩ አጋር አካላት ጋር በመተባበር በማህበረሰቡ ውስጥ የሚያመጣቸውን እነዚህን ሁለንተናዊ የልማትና የመልካም አስተዳደር ለውጦች አጠናክሮ ይቀጥላል!!

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top