ከ7 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ለተጋላጭ ሴቶችና ልጃገረዶች ድጋፍ ተደረገ!!

የአማራ ሴቶች ማህበር ከተባበሩት መንግሥታት የሕፃናት መርጃ ድርጅት (UNICEF) ጋር በመተባበር በሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅ ዙሪያ እና ዳባት ወረዳዎች ሥርዓተ-ፆታን መሠረት ያደረገ ጥቃት መከላከልና ምላሽ መስጠት ፕሮጀክት እየተገበረ ይገኛል።

በዚሁ ፕሮጀክት አማካኝነት ለ200 ለሚሆኑ ተጎጂ ሴቶችና ልጃገረዶች መሠረታዊ ፍላጎቶቻቸውን ለማሟላት ታስቦ የተዘጋጀ የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ድጋፍ ተደርጓል።

በድጋፉ ፒጃማ߹ ሳሙና߹ ፎጣ ߹ የእጅ ባትሪ እና ማበጠሪያ߹የሴቶች የንፅህና መጠበቂያ (ሞዴስ)
የፀጉር ቅባት ߹የውሀ ማጠራቀሚያ ጀሪካ እና ሌሎች አስፈላጊ ቁሳቁሶች ድጋፍ መልክ ተሰጥቷል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ለ300 ተጋላጭ ሴቶችና ልጃገረዶች ወደ ጤና ተቋማት መጥተው በሚታከሙበት ወቅት ተገቢውን አገልግሎት በቀላሉ ማግኘት እንዲችሉ በማሰብ የንፅኅና መጠበቂያ ቁሳቁስ በሆስፒታል ውስጥ ለሚገኙ የአንድ ማእከል አገልግሎቶች ድጋፍ ተደርጓል።

በአማራ ሴቶች ማህበር የUNICEF ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ ዮናስ ተረፈ እንዳስታወቁት ማህበሩ በቀጣይም በሞባይል አውትሪች (Mobile Outreach) ወይም ቤት ለቤት እየተንቀሳቀሱ ተጋላጭ ሴቶችን ለሚደግፉ ባለሙያዎች የሚሆንና ለ300 ተጋላጮች የሚደርስ የንፅኅና መጠበቂያ ቁሳቁስ ዝግጁ መደረጉን ገልጸዋል።

በጥቅሉ ለ800 ተጋላጭ ሴቶችና ልጃ ገረዶች ከ7 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ መደረጉን ተናግረዋል ፡፡

Telegram _ https://t.me/Awaoffice
Facebook:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100079616269030
Tiktok @awa79100
Website https://www amharawomenasso.org.et

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top