የአማራ ሴቶች ማህበር የ2018 በጀት አመት እቅድ አፈፃፀም ግምገማና የ2019 በጀት አመት እቅድ ትውውቅ መድረክ በደብረ ማርቆስ ከተማ ተካሄደ።
ጳጉሜ 2/2018ዓ.ም(ደብረ ማርቆስ ኮሙኒኬሽን): በእቅድ አፈፃፀም ግምገማውና የእቅድ ትውውቅ መድረኩ ከጎጃም ቀጠና ዞኖች የመጡ የማህበሩ አባላት እና ሃላፊዎች ተሳትፈዋል።
ማህበሩ የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማጎልበት የሴቶች ሰባዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ለማረጋገጥ አላማ አድርጎ እየሰራ ይገኛል።
በማህበሩ አሁን ላይ ከ 2 ሚሊየን በላይ አባላትን ማፍራት መቻሉን በቀረበው የ2018 እቅድ አፈፃፀም ተገልጿል።
የአማራ ሴቶች ማህበር ዋና ዳሬክተር ገነት ወንድሙ እንደገለፁት ማህበሩ ለተለያዩ ችግሮች ተጋለጭ የሆኑ ሴቶችን ወደ አላስፈላጊ ችግር ውስጥ እንዳይገቡ በኢኮኖሚ ተጠቃሚ እንዲሆኑ እያደረገ ይገኛል ብለዋል።
ከ19 ሺ በላይ ለሚሆኑ ሴቶች ከወለድ ነፃ ብድር በመስጠት ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ገልፀዋል።
ሴቶች በማህበራዊ ፓለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በጤና፣ በትምህርት፣ የሴቶችን ጥቃት በመከላከል እና የህግ ከለላ እንዲያገኙ እየተሰራ መሆኑንም ዋና ዳይሬክተሯ አስገንዝበዋል።
መልካም አስተዳደር እንዲሰፍን እና በሁሉም ዘርፍ የሴቶችን ተሳትፎ ለማሳደግ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው ብለዋል።
የአማራ ሴቶች ማህበር በ2019 በጀት አመት አባላቱን በማሳደግ በክልል የሚገኙ የሴቶችን ተሳትፎን ማሳደግና ተጠቃሚ ለማድረግ እንደሚሰራ ወ/ሮ ገነት ገልፀዋል።
የማህበሩ የቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሮ ዳርእስከዳር ጌቴ ማህበሩ ከሌሎች አጋር አካላት ጋር በመቀናጀት የሴቶችን ተጠቃሚነት ለማሳደግና የሴቶችን ጥቃት ለመካላከል እየሰራ ይገኛል ብለዋል።
ሴቶች በመደራጀት በየአካባቢያቸው ሰላም እንዲሰፍን ሚናቸውን በመወጣት ለሃገር ሰላም እና እድገት የበኩላቸው አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ ለማድረግ እየተሰራ ስለመሆኑም ተናግረዋል።
የመድረኩ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት ማህበሩ ሴቶች ተደራጅተው ለመብታቸው መጠበቅና በሁሉም ዘርፍ የሴቶችን ተሳትፎ ለማሳደግ የሚሰራ በመሆኑ ሌሎች ሴቶችም በማህበሩ አባል መመሆን በተለያዩ ዘርፎች ተጠቃሚ መሆን እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል።






Telegram _ https://t.me/Awaoffice
Facebook:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100079616269030
Tiktok @awa79100
Website https://www amharawomenasso.org.et
See less
