Message from women association

ወ/ሮ ሁሉአየሽ አወቀ

የማህበሩ ም/ዳይሬክተር

የማኅበሩ ተግባር እና ኃላፊነት፦

ማኅበሩ ዓላማዎቹን ለማሳካት ከዚህ በታች የተመለከቱት ዝርዝር ተግባርና ሃላፊነቶች ይኖሩታል፡-

  • ሴቷ መሠረታዊ ትምህርት፣ ስልጠናና የሥራ ዕድል የምታገኝበትን ሁኔታ ያመቻቻል፤
  • በአገሯ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ረገድ ንቁ ተሳትፎ እንዲኖራት ያበረታታል፤
  • ሴቷን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የተለያዩ የስልጠናና የአቅም ግንባታ መርሃ-ግብሮችንና ፕሮጀክቶችን ይዘረጋል፣ ያስፈፅማል፤
  • ዓላማዎቹን ከሚደግፉ መሰል የልማትና የግብረ-ሰናይ ድርጅቶች ጋር ግንኙነቶችን ያደርጋል፣ ተባብሮ ይሠራል፤
  • የማኅበሩን አባላት በተዘዋዋሪ ብድር አገልግሎት፣ በቀጥታ የገንዘብ ድጋፍ እና በመሳሰሉት መንገዶች በማገዝ ከድህነት እንዲወጡ ጥረት ያደርጋል፤
  • መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት እና ህዝቡን በማስተባበር ወይም በህዝባዊ መዋጮ ማኅበሩን በገቢ ያጠናክራል፤

ዜና | News

Selective Services

ከማህበሩ ጠቅላላ አባላት 9ዐ% የሚሆኑ የገጠር ሴቶችን የኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ አንዱ ነው፡፡

ማህበሩም  በ26 ዓመት ጉዞው ውስጥ በገጠር ሴቶች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ያመጣው ለውጥ ሴቶች በፆታ አደረጃጀታቸው በመጠቀም በግብርና ፖሊሲው ውስጥ በግልጽ የተመለከተውን የገጠር ሴቶችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት በግብርናው ዘርፍ ለማረጋገጥ በአደረጃጀታቸው ፖሊሲውንና ሴቶችን በማቀራረብ ፖሊሲውን ተጠቅመው እንዲያለሙ በማድረግ የተሻሻለ ግብአትና ቴክኖሉጂ እንዲጠቀሙ በላቀ ደረጃ ምርት እንዲጨምሩ በመደገፍ አባላት የመሬት ተጠቃሚነት ማረጋገጫ ሰርትፊኬት በግንባር ቀደምነት እንዲያገኙና ሌሎች ሴቶችን እንዲቀሰቅሱ በማድረግ በሴቶች የ1ለ5 እና የሴቶች የልማት ህብረት ቡድን አደረጃጀት ውስጥ የመሪነት ሚናቸውን በመወጣት የግብርና እድገትና የምግብ ዋስትናን በሚያረጋግጡ ኘሮግራሞች አባላት ሴቶች በቀደምትነት እንዲሳተፉ በአደረጃጀታቸው በመቀስቀስና በማስተማር፤ በእንስሳት ሀብት ሥራዎች ማለትም /ሴቶች በደሮ ልማት ፖኬጅ፣ በእንስሳት እርባታ እና ማድለብ፣ በጓሮ አትክልት ሥራዎች በመኖሪያ አካባቢያቸው ላይ እንዲሰሩ በመደገፍ፣ በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ እና በአረንጓዴ ልማት ኘሮግሞች ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል፡፡

ለልማት መፋጠን ቁልፍ ሚና በሚጫወተው ትምህርት በአገራችን ብሎም በክልላችን ከተጀመረ የቆየ ቢሆንም እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ስርጭቱ በከተሞች አካባቢ ተወስኖ ነበር፡፡ ይህን ሁኔታ ለመለወጥ ማህበሩ ባለፉት ሁለት አስርት አመታት በርካታ ተግባራትን እንዳከናወነ ይታወቃል፡፡ አባላት የተፈጠረውን የትምህርት መስፋፋት እና ተደራሽነት ምቹ ሁኔታ በመጠቀም እናቶች ለትምህርት የደረሱ ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት በማስገባት ለሴቶች ልጆች የጥናት ጊዜ በመስጠት ውጤታማ እንዲሆኑ በማገዝ ትምህርታቸውን ለሚያቋርጡ ለሚደግሙና የኢኮኖሚ ችግር ላለባቸው ሴት ተማሪዎች የማቴሪያል የቴክኒክ ድጋፍ በማድረግ በትምህርታቸው ጥሩ ውጤት የሚያመጡ ሴት ተማሪዎችን ማበረታታት እና እውቅና በመስጠት፣ መንግስት በዘረጋው የተቀናጀ ተግባር ተኮር የጐልማሶች ትምህርት ውስጥ የመደበኛ ትምህርት እድል ያላገኙ ሴቶችን ተጠቃሚ የሚያደርግ በየአካባቢያቸው የተፈጠረው እድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ሁኔታዎችን ማመቻቸት፣ ማህበሩ የተለያዩ ኘሮጀክቶችን በመቅረጽና ከአማራ ሴቶች ፌደሬሽን ጋር በመቀናጀት በመጀመሪያ ዲግሪ 84 ሴቶችን እንዲሁም በሁለተኛ ዲግሪ 58 በድምሩ 142 የማህበሩ አመራር እና አባላት ሴቶችን በረጅም ጊዜ ስልጠና የትምህርት እድል እንዲያገኙ ተደርጓል፡፣ ለችግረኛ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ በማድረግ፣ በትምህርት ተቋማት ውስጥ የሚማሩ ሴት ተማሪዎች በፆታዊ ትንኮሳና ጥቃት ለመጠበቅ የአቻለአቻ ውይይቶችን በማመቻቸት በመንግስት የተጀመሩ ሥራዎችን በመደገፍ እና በማጠናከር፣ በት/ቤቶች የሴቶችን ተሳትፎና ውጤታማነት ለማሳደግ የተቋቋሙ ክበባትን በገንዘብ ፣ በተለያዩ ስልጠናዎችና በቁሳቁስ በማገዝ ተሳትፏቸውን ማሳደግ ተችሏል፡፡

 

የአማራ ሴቶች ማህበር ከሚሰራቸው ስራወች ውስጥ ሴቶች ለመብት እና ጥቅሞቻቸው መከበር ሴቶችን አደራጅቶ ከማንቀሳቀስ በተጨማሪ የውሳኔ ሰጭነት ሚናቸውን እንዲጎለብት ማድረግ ሲሆን ሴቶቹ በጾታ ማህበራቸው አማካኝነት በውይይታቸው ሃሳብን በነጻነት መግለጽ፤መሪወቻቸውን በመምረጥ ፤አባሎቻቸውን በመምራት በአካባቢያቸው ልማት እና የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ላይ ባለቤት እንዲሆኑ አቅማቸውን በማጎልበት እና የውሳኔ ሰጭነት እና የአመራር ሰጭነት ብቃታቸውን በማሳደግ የአመራር ክህሎታቸውን እንዲያዳብሩ በርካታ ስራወች በመሰራታቸው እና ሴቶች ብቁ በመሆናቸው ለተለያዩ ለመንግስት ሃላፊነቶች ተመራጭ እንዲሆኑ አድርጓል፡፡በዚህም በርካታ ሴቶች ከማህበራቸው ባገኙት አቅም በቤታቸው ጉዳይ በጋራ ከመወሰን አልፈው በተለያዩ የሃላፊነት እና የውሳኔ ሰጭነት ቦታወች እንዲበቁ አድርጓል የሴቶችን ጥቅም የሚስከብሩ ህጎች እንዲዎጡ ታግሏል፡፡ማህበሩም በየደረጃው ባሉ የህዝብ ምክር ቤቶች የሴቶች ንቁ ተሳትፎ እና የውሳኔ ሰጭነት አቅም እንዲጎለብት እና የተሳትፎ መጠናቸው እንዲጨምር በማድረግ በፍትህ አካላት የውሳኔ ሰጭነት ቦታወች የስራ መደቦች፤( በመደበኛ እና በማህበራዊ ፍ/ቤቶች) ተሳትፏቸው እንዲጨምር፤እንዲሁም በየጊዜው በሚካሄዱ አካባቢያዊ እና አገራዊ ምርጫወች ከምንም ጫና ነጻ ሁነው በመምረጥ እና በመመረጥ እንዲሁም እንደ ሲቪክ ማህበር የምርጫውን ታማኒነት በመታዘብ ሴቶች ለዲሞክራሲ መጎልበት ሚናቸውን በመወጣት እና መሪ ሴቶችን የሚያወጣ ሁኖ በማገልገሉ በሂደቱም ተጠቃሚ እንዲሆኑ  እየሰራ ይገኛል፡፡ በመሆኑም ምንም እንኳን በሚፈለገው መንገድ የደረሰ ነው ባይባልም በተለያየ የመንግስትም ሆን የፖለቲካ አመራረነት ላይ ያሉ ሴቶች እንደመነሻ ሆኖ እያገለገለ ነው፡፡

 

Contact Us

Please enable JavaScript in your browser to complete this form.
name
e-mail addiress
comments

Partners

Scroll to Top