የአማራ ሴቶች ማህበር ከHelvetas Ethiopia ጋር በመተባበር ለተመረጡ የህብረተሰብ ክፍሎች በአሳታፊ እቅድ ዙሪያ የግንዛቤ ፈጠራ ስራ መስራቱን አሳዎቀ፡፡

የአማራ ሴቶች ማህበር ከHelvetas Ethiopia ጋር በመተባበር ለተመረጡ የህብረተሰብ ክፍሎች በአሳታፊ እቅድ ዙሪያ የግንዛቤ ፈጠራ ስራ መስራቱን አሳዎቀ፡፡

የአማራ ሴቶች ማህበር ከHelvetas Ethiopia ጋር በመተባበር  በማዕ/ጎንደር ዞን ምዕ/ደንቢያ፣አለፋ፣ጣቁሳና ጎንደር ከተማ የአማራ አካባቢያዊ ፕሮጀክት የተቀናጀ ማህበረሰብ አቀፍ እቅድ ማሳቀድ ስራ እያከናወነ ይገኛል፡፡

በመሆኑም  የአማራ አካባቢያዊ ፕሮጀክት ፕሮጀክቱ በሚተገበርባቸው አካባቢዎች ለባለድርሻ አካላት፣ለወረዳ የእቅድ ሙያተኞች፣የመንግስት ሀላፊዎች፣የምክር ቤት አባላት፣የፕሮጀክቱ አመቻቾች እንዲሁም ለ3360 ለተመረጡ የህብረተሰብ ክፍሎች በዚህ ስድስት ወር ውስጥ  ስልጠና መሰጠቱን የገለፁት በማህበሩ የፕሮጀክት አስተባባሪ የሆኑት አቶ ጌጡ ብርሀን ናቸው፡፡

 አቶ ጌጡ ብርሀን አክለውም በ4 ወረዳና በ60 ቀበሌዎች ህብረተሰቡን ያሳተፈ እቅድ በማሳቀድ በቀበሌ ምክር ቤት የማፀደቅ ስራ እንዳከናዎኑ ገልፀዋል፡፡

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top