
ጥቃት ለደሰረሰባቸው ሴቶችና ህፃናት ማረፊያ አገልግሎት የሚውል የህንፃ ግንባታ የስራ ጉብኝት ተደረገ፡:
የማህበሩ ምክትል ዳይሬክተር ወ/ሮ ሁሉአየሽ አወቀና የማህበሩ ሰራተኞች በጋራ በመሆን በደቡብ ጎንደር ዞን ነፋስ መውጫ ከተማ እየተሰራ የሚገኘውን የእናቶችና ህፃናት ማቆያ ህንፃ ሰኔ 07/2015ዓ.ም የስራ ጉብኝት አድርገዋል፡፡
ማህበሩ ከተባበሩት መንግስታት የስነ-ህዝብ ፈንድ/UNFPA/ ጋር በመተባበር ደባርቅ ደሴ ኮምቦልቻ ደብረብርሀንና ነፋስ መውጫ ከተሞች ጥቃት የደረሰባቸው እናቶችና ህፃናት ማቆያ የሚሆን ህንፃ እያሰራ መሆኑ የሚታወስ ነው፡፡
ም/ዳይሬክተሯ አያይዘውም ለደቡብ ጎንደር ዞን ነፋስ መውጫ ከተማ አማራ ሴቶች ማህበር ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ የስራ መርጃ መሳሪያዎችን የፋይል ሸልፍ፤ ፕሪንተር ፤ወረቀትና ሌሎች ማቴሪያሎች ድጋፍ አድርገዋል፡፡
tkyiou[