የስነ-ልቦናና ማህበራዊ ድጋፍ አሰጣጥ በተመለከተ ስልጠና ተሰጠ
የአማራ ሴቶች ማህበር ከተባበሩት መንግስታት የስነ ህዝብ ፈንድ/UNFPA/ ጋር በመተባበር በጦርነት ወቅት የሚከሰቱ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችና ፆታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶችን መከላከልና ምላሽ መስጠት ፕሮጀክት በደብረብርሀን፡ደሴ፡ደባርቅ፡ኮምቦልቻና ንፋስ መውጫ ከተሞች እየተተገበረ ይገኛል ፡፡
በመሆኑም ይህ ፕሮጀክት በባህርዳር ከተማ ግንቦት 8/2015ዓ.ም ከ5ቱ የፕሮጃክት አካባቢዎች ለመጡ ከሴቶችና ህፃናት ማህበራዊ ጉዳይ ፅ/ቤት የማዳራጃ ባለሙያዎች የአማራ ሴቶች ማህበር የቦርድ አመራሮች ከጠቅላይ አቃቢ ህግና ፖሊስ የሴቶች ተወካዮች በተጨማሪ የፕሮጀክቱ ጉዳይ አያያዝ ባለሙያዎችና ሶሻል ወርከሮች በተገኙበት የስነ-ልቦናና ማህበራዊ ድጋፍ ለተጎጅዎች መስጠት የሚያስችል ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል፡፡
ስልጠናውን የሚሰጡልን የአማራ ክልል የ/UNFPA/ GBV program Analyst ወ/ሮ አዳነች ሽፈራው
የአማራ ሴቶች ማህበር የ/UNFPA/ የሰሜን ጎንደር ዞን የስነ-ልቦና አማካሪና
የአማራ ሴቶች ማህበር የ/UNFPA/ ረዳት ፕሮግራም አስተባባሪ የሆኑት አቶ መሳፍንት ነጋሽ ናቸው
fgfhgjhj]hgkk