የአማራ ሴቶች ማህበር በደባርቅ ከተማ ያስገነባው የሴቶች ምቹ ማረፊያ ህንፃ ስራ ጀመረ።

ማህበሩ ከUNFPA ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ በሁለት ዞኖችና በሶስት ከተማ አስተዳደሮች በሰ/ጎንደር ደባርቅ፣ በደ/ጎንደር ነፋስ መውጫ እንዲሁም በደብረብርሀን፣ደሴና ኮምቦልቻ ከተሞች ለፆታዊ ጥቃት ተጋላጭ ለሆኑ ሴቶችና ልጃገረዶች ከደረሰባቸው ጥቃት በላይ በማህበረሰባችን ውስጥ ባለ የአመለካከት ችግር ምክንያት ወደ ህክምና እየተመላለሱ መታከም ለማይችሉ ሴቶች ማገገሚያ እንዲሆን፣ በጊዜያዊነት በፆታዊ ጥቃት ችግር ምክንያት ማረፊያ ለሚቸገሩ እንደመጠለያ ማገልገልና የስነልቦና ድጋፍ አገልግሎት መስጫ ማእከል ሆኖ እንዲያገለግል  መገንባቱ ይታወሳል።በመሆኑም በሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅ ከተማ የተገነባው ህንፃ  አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።

መረጃውን ያደረሰን በአማራ ሴቶች ማህበር UNFPA ፕሮጀክት የደባርቅ ከተማ የስነ-ልቦና አማካሪ ባለሙያ አቶ ደሌ ካሳ ናቸው።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top