ጷግሜ 1/2016ዓ.ም የአማራ ሴቶች ማህበር ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሮ ዳርእስከዳር ጌቴ ማህበሩ ከተባበሩት መንግስታት የስነ-ህዝብ ፈንድ /UNFPA/ ጋር በመተባበር በሚተገብረው ፕሮጀክት የስምንት ወር እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ ላይ ተገኝተው ባስተላለፋት መልዕክት ሀገራችን ብሎም ክልላችን ብዙ ችግሮችን እያስተናገደች እንደሆነ አውስተው ችግሩን ለመቅረፍ በመንግስት፣ በማህበረሰቡ እና በአጋር አካላት ተሳትፎ በርካታ ስራዎች ቢሰሩም አሁን ላይ በክልላችን ያለው የተፈናቃዮች ቁጥር መጨመር፣ያለው የፀጥታ ችግር ፆታን መሰረት ያደረገ ጥቃት እንዲጨምር ምክንያት እንደሆነ ገልፀዋል። ችግሩን ለመከላከልና ምላሽ ለመስጠት UNFPA ጋር በመተባበር በደብረብርሀን፣ንፋስ መውጫ፣ደባርቅ ደሴና ኮምቦልቻ ከተሞች ላይ በጋራ በመስራት ውጤት እንደተመዘገበ ገልፀው ይህ ተግባራችን የሴቶችና ልጃገረዶች ችግር ከማቃለሉ በተጨማሪ አጋር ድርጅቶች ከማህበሩ ጋር የመስራት ፍላጎትን ጨምሯል ብለዋል።
የUNFPA SRH/GBV program Analysit አቶ ጌጡ ቸርነት በፕሮግራሙ ተገኝተዋል።ድርጅታቸው ከአማራ ሴቶች ማህበር ጋር 4 አመት በላይ አብረው እንደሰሩ ተናግረው ክልሉ ውስጥ ፆታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች ላይ ከሚሰሩ ተቋሞች መካከል ጠንካራው እንደሆነ ገልፀው አብረው በመስራታቸው ደስተኞች ነን ብለዋል።
በፕሮግራሙ የሁሉም ከተሞችና የክልሉ ሪፓርት ቀርቦ በጉዳይ አያያዝ፤የተደረጉ የቀጥታና የገንዘብ ድጋፎች፤ በግልና በጋራ የተሰጡ የስነ-ልቦና ድጋፎች የቅብብሎሽ ስራዎች ፆታን መሰረት ያደረገ ጥቃት መከላከልና ምልሽ መስጠት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ ላይ የነበሩ ጥንካሬዎችና ድክመቶች ተነስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል ።